ደረጃ በተሰጠዉ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ እያንዳንዱ መራጭ ፕሮጀክቶችን በምርጫ ቅደም ተከተል ደረጃ ይሰጣል። አንድ ፕሮጀክት መራጩ በሰጠው ደረጃ ላይ በመመስረት ነጥቦችን ይቀበላል። አሸናፊ ፕሮጀክቶች የሚመረጡት የገንዘብ አቅሙ ገደብ እስኪያልቅ ድረስ በተሰበሰቡት ነጥቦች በቅደም ተከተል ነው።
የዋይት ሴንተር ማህበረሰብ ማዕከል – ግንባታ ፈንድ
የዋይት ሴንተር ማህበረሰብ ማዕከል “የተስፋ፣ አንድነት እና አባልነት”ቦታ ይሆናል። ፕሮጀክቱ የሚያካትተዉ ለወጣቶች እና ቤተሰቦች የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶች፣ የምግብ ፍትህ ፕሮግራሞች፣ የወጣቶች ማህበረሰብ ማደራጀት፣ ከትምህርት ቤት በኋላ አንቅስቃሴዎች፣ የሥራ ፈጠራ ፕሮግራም፣ የመጀመሪያ ልጅነት ጊዜያት ትምህርት አገልግሎቶች፣ እና ሌላ የማህበረሰብ ግንኙነት ፕሮግራሞች። ይህ ለዋይት ሴንተር ማህበረሰብ ማዕከል በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $750,000