ደረጃ በተሰጠዉ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ እያንዳንዱ መራጭ ፕሮጀክቶችን በምርጫ ቅደም ተከተል ደረጃ ይሰጣል። አንድ ፕሮጀክት መራጩ በሰጠው ደረጃ ላይ በመመስረት ነጥቦችን ይቀበላል። አሸናፊ ፕሮጀክቶች የሚመረጡት የገንዘብ አቅሙ ገደብ እስኪያልቅ ድረስ በተሰበሰቡት ነጥቦች በቅደም ተከተል ነው።
የመድረክ ላይ ትወናዎች – ፕሮግራም
ከትምህርት ቤት በኋላ የቲያትር/ኣርቶች ፕሮግራም ስልጠና ፕሮግራም። ለ 50 ዕድሜያቸዉ ከ 10-17 የሆኑ ወጣቶች ነጻ የ10 ወር ፕሮግራም። ይህ ለመድረክ ላይ ትወናዎች በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $75,000
Select አስወግድ
አረንጓዴ ትምህርት – አዲስ ጅምር
ኦርጋኒክ የጓሮ አትክልት ፕሮግራም ለተማሪዎች እና ማህበረሰብ፣ ለዋይት ሴንተር ምግብ ባንክ አግባብነት ያለዉ ኦርጋኒክ ምርት ማቅረብ። ስጋት ላይ ለሆኑ ወጣቶች ለበጋ የጓሮ አትክልት ፕሮግራም ድጋፍ። ይህ ለአዲስ ጅምር ትምህርት ቤት በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $66,000
በእንጨት ቤት የወጣት ማእከል ፕሮግራሚንግ
እድሜአቸው ከ 14-18 አመት ለሆኑ ወጣቶች የመግቢያ ቦታን ለማቅረብ ከእንጨት ቤት ውጪ የሚሰራውን የወጣቶች ፕሮግራም ማሻሻል • እድሜአቸው ከ 14-18 አመት ለሆኑ ወጣቶች በሙሉ ነጻ ነው • ከትምህርት-በኋላ የሚኖሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች • የበጋ ፕሮግራም
ግምታዊ ዋጋ: $50,000
የድምጽ ሰጪዎች ትምህርት
የመራጮች ትምህርትና ተደራሽነት፡፡ የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በመራጮች ምዝገባና የድምጽ መስጫ ወረቀት እንዴት መረዳት እንደሚችሉ ግንዛቤ ማስጨበጥ፡፡
ግምታዊ ዋጋ: $40,000
የወልቨሪን ምርጫ – ገንዘብ ድጋፍ
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ወይም በታሪክ ያነሰ አገልግሎት ያገኙ ቤተሰብ ወጣቶች የቅርጫት ኳስ ፕሮግራም ተሳትፎ ይደግፋል። ተማሪዎች (3-11 ክፍሎች) በሳምንታዊ ልምምዶች፣ አካባቢያዊ ዉድድሮች፣ እና የ አጋር ጣቢያዎች ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋሉ። ፕሮግራሙ የትምህርት ድጋፍ፣ ምክር፣ እና የመበልጸጊያ ዕድሎችን ያካተተ ነዉ። ይህ ለወልቨሪን ምርጫ በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $30,000
የኔፓንትላ ባህላዊ ኣርት ፕሮግራም
ላቲንክስ እና ዋይት ሴንተር ማህበረሰብ ለሆኑ ኣርቲስቶች ለኔፓንትላ ባህላዊ ኣርት ቦታ አቅም ግንባታ እና ፕሮግራም ለማቅረብ የገንዘብ ድጋፍ። ይህ ለኔፓንትላ ማዕከል በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $150,000
የዋይት ሴንተር ሃይትስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቤተሰብ ድጋፍ ምንጭ ማዕከል
በሶማሊኛ፣ ቬትናሚዝ እና ስፓኒሽ ተግባቦትን፣ አቅም ግንባታ፣ የድጋፍ ምንጭ ማዕከል አቅርቦቶች በማቅረብ ቤተሰቦችን ለመደገፍ ለሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሠራተኞች የገንዘብ ድጋፍ። ይህ ለዋይት ሴንተር ሃይትስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $25,000
የተፈናቃይ ዘጋቢ ፊልም - ፊልም
በዋይት ማእከል/ኖርዝ ሃይላይን ያልተካተቱ አካባቢዎች መፈናቀል የሚያስከትለውን ውጤት የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም እንዲሰራ ለመደገፍ የሚሆን ገንዘብ፡፡
ግምታዊ ዋጋ: $83,000
የተስፋ ስጦታዎች
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ ወይም በታሪክ ያነሰ አገልግሎት ላገኙ የማህበረሰብ አባላት ድጋፍ ምንጮችን የሚያቀርብ ለተስፋ ስጦታዎች ፕሮግራም የአቅም/ማህበረሰብ ግንባታ ለመደገፍ የገንዘብ ድጋፍ። ይህ ለተሰፋ ስጦታዎች በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
ግምታዊ ዋጋ: $175,000
የድህነት ሰራዊት - መስሪያ ቦታ
በኋይት ሴንተር/ኖርዝ ሃይላይን ለሚኖሩ ወጣቶች ለሚሰጥ ነጻ የ STEM ፕሮግራም የሚሆን ገንዘብ፡፡
ግምታዊ ዋጋ: $48,600
ጌምሼፕ
በአትሌቲክ የተመሰረተ ስልጠና፣ ጥንካሬ እና ዝግጅት ዉስጥ የ አንቅስቃሴዎችን መርሆችን የሚያስተምር ነጻ የ ከትምህርት ቤት በኋላ የሰዉነት ማጎልመሻ ትምህርት ፕሮግራም። ከ 8-17 ዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶችን የሚያገለግል፣ የትምህርት ቤት ዓመት/የበጋ ካምፕ። ይህ ለጌምሼፕ በቀጥታ የተሰጠ ድጋፍ ነዉ።
የአእምሮ ጤና - ለሃዘን የሚደረግ ድጋፍ
ለወጣቶች፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች የፈውስ ቡድኖች/መስሪያ ቦታ፡፡
ግምታዊ ዋጋ: $32,500
የወላጅ ትምህርት/ተሟጋች ድጋፍ
በትምህርት ቤቶች ውስጥ የወላጅ ትምህርትን በገንዘብ መደገፍ ፣ ወላጆች ለልጆቻቸው እንዲሟገቱ ብቃት ይሰጣቸዋል::
ግምታዊ ዋጋ: $60,000