ደረጃ በተሰጠዉ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ እያንዳንዱ መራጭ ፕሮጀክቶችን በምርጫ ቅደም ተከተል ደረጃ ይሰጣል። አንድ ፕሮጀክት መራጩ በሰጠው ደረጃ ላይ በመመስረት ነጥቦችን ይቀበላል። አሸናፊ ፕሮጀክቶች የሚመረጡት የገንዘብ አቅሙ ገደብ እስኪያልቅ ድረስ በተሰበሰቡት ነጥቦች በቅደም ተከተል ነው።
የዋይት ሴንተር ሃይትስ አንደኛ ደረጃ የመጫወቻ ሜዳ፡ ከማህበረሰብ ጋር ማደግ
የትምህርት ቤት የእግር ኳስ መርሃ ግብርን ለመደገፍና ለማህበረሰብ አገልግሎት የውጪ ቦታን ለመፍጠር ያለውን የመጫወቻ ሜዳ ያሻሽሉ። ለዋይት ሴንተር ሃይትስ አንደኛ ደረጃ ለሃይላይን ት/ቤት ዲስትሪክት ቀጥተኛ ሽልማት ለአካባቢው ቤተሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀና አሳታፊ ቦታ ይስጡ። ለልጆች የሚጫወቱበት አዲስ ቦታ ጠንካራ ማህበረሰብ ለመገንባት ይረዳል።
ግምታዊ ዋጋ: $700,000
ቦታ: 10015 6th Avenue SW, Seattle WA 98146
ሪቭታላይዝ፡ ኤቨርግሪን የውሃ ማዕከል
የሕንፃ / መገልገያ እድሳትን ይደግፉ። ለኤቨርግሪን አኩዋትክ ሴንተር ቀጥተኛ ሽልማት የውሃ ማዕከል አገልግሎት ላልተሰጠ ማህበረሰብ በጣም የሚፈለግ የመዝናኛና የትምህርት ቦታ ይሰጣል። በሁሉም ዕድሜ ላሉ ነዋሪዎች ጤናን፣ ደህንነትንና የውሃ ደህንነትን ያበረታታል። ይህንን ፋሲሊቲ ማደስ የውሃ ፕሮግራሞችን ፍትሃዊ ተደራሽነት ያቀርባል፣ የማህበረሰብ ተሳትፎን ያሳድጋል፣ እንደዚሁም የህብረተሰቡን አጠቃላይ የህይወት ጥራት ያሳድጋል።
ግምታዊ ዋጋ: $750,000
ቦታ: 606 SW 116th Street, Seattle WA 98146
"ካስኬድ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ የብዝሃ ቋንቋ አንባቢ ቦርድ ለማህበረሰብ ግንኙነት "
በትምህርት ቤት ንብረት ላይ አዲስ LCD ባለብዙ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰብ አንባቢ ሰሌዳ ይጫኑ። ለካስኬድ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለሃይላይን ት/ቤት ዲስትሪክት ቀጥተኛ ሽልማት ሁሉም ቤተሰቦች እንዲያውቁና እንዲሳተፉ እርዷቸው፣ የበለጠ አካታች የትምህርት ቤት አካባቢን እንዲደግፉና በትምህርት ቤቱ እንደዚሁም በልዩ ልዩ ማህበረሰቡ መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ያድርጉ።
ግምታዊ ዋጋ: $60,000
ቦታ: 11212 10th Avenue SW, Seattle WA 98146