እርስዎ
0 / 0
ፕሮጀክቶችን መርጠዋል።

ይህ ቅድመ ማሳያ ብቻ ነው። የእርስዎ የምርጫ ድምጽ አይመዘገብም።

መመሪያዎች

  1. መደገፍ የሚፈልጓቸውን ፕሮጀክቶች ይምረጡ። እስከ 5 ፕሮጀክቶች መምረጥ ይችላሉ።
  2. ለማስረከብ ዝግጁ ሲሆኑ "የእኔን የምርጫ ድምጽ አስገባ"የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ማስታወሻ: እነዚህ ፕሮጀክቶች በዘፈቀደ ቅደም ተከተል የተዘረዘሩ ናቸው።



የተሻለ የትራፊክ ፍሰት ያላቸው የአውቶብስ ማቆሚያዎች፦ የብስክሌት ነጂዎች እና የአውቶብስ አሽከርካሪዎች ደኅንነትን ያሻሽላል

'የተሻለ የትራፊክ ፍሰት ያለው የአውቶብስ ማቆሚያ' የሚባለው አውቶብሱ በመጓጓዣ መንገዱ ላይ እንዲቆም የሚያስችል፣ የአውቶብሱን እና የእግረኛ መንገዱን ደግሞ በብስክሌት መንገዱ ለይቶ ማቆየት የሚያስችለው አሠራር ነው። ይህ ፕሮጀክት ለአስተማማኝ ጉዞዎችየሚሆኑ ሁለት የተሻለ የትራፊክ ፍሰት ያላቸውን የአውቶብስ ማቆሚያዎች የሚገነባ ሲሆን፣ ግንባታውም እግረኛዎችን፣ በብስክሌት የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እና የአውቶብስ ተጠቃሚዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ግምታዊ ዋጋ: $250,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

ቤት ለሌላቸው ነዋሪዎች የሚሆኑ ተጨማሪ አቅርቦቶች

ቋሚ መኖሪያ ቤት የሌላቸውን ሰዎች ለመርዳት የሚሆኑ እንደ ካልሲዎች፣ ኮፍያዎች፣ ጓንቶች፣ የእጅ ማሞቂያዎች፣ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች እና ሌሎችንም ቁሳቁሶች ጨምሮ ለዚህ ዓላማ በተቋቋሙ ፕሮግራሞች አማካኝነት ወሳኝ አቅርቦቶችን የማቅረብ ሥራ።

ግምታዊ ዋጋ: $50,000

ቦታ: ከተማ-አቀፍ

   

ዥዋዥዌ ያለው Teen Oasis (የታዳጊዎች መዝናኛ)

Cambridge ውስጥ Teen Oasis (የታዳጊዎች መዝናኛ) እንገንባ! በመጠለያ የተሸፈነ፣ የሚያበሩ ዥዋዥዌዎች ያሉት፣ ዝግጅቶች በመርሃ-ግብር የሚዘጋጁበት ለታዳጊዎች የሚሆን ቦታ። ይህ ፕሮጀክት ታዳጊዎች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉበት፣ ከቤት ውጭ የሚዝናኑበት እና የሚገናኙበት ምቹ የሆነ ቦታ ይሰጣቸዋል።

ግምታዊ ዋጋ: $400,000

ቦታ: Donnelly Field

   

ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የሚሆኑ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች

ባለቤትነታቸው የከተማው በሆኑ ሦስት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና በከተማው በሚወሰኑ ሌሎች ቦታዎች ላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች የመግጠም ሥራ። ተጨማሪ የሕዝብ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ሲሠሩ፣ የአየር ጥራት ይሻሻላል፣ አካባቢያችንንም ይጠቅማል።

ግምታዊ ዋጋ: $350,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

አይጦችን ለመቀነስ የሚያግዙ ስማርት ወጥመዶች (ስማርት ሳጥኖች)

አይጦችን ለመቀነስ እና መረጃ ለመሰብሰብ የሚሆኑ 100 ተጨማሪ Smart Boxes “ስማርት ሳጥኖችን” (የአይጥ ወጥመዶችን) የመግዛት፣ የማስቀመጥ እና በይዞታቸው ጠብቆ የማቆየት ሥራ። እነዚህን ወጥመዶች መጨመር፣ በአሁኑ ጊዜ እየተወሰዱ ያሉትን የነፍሳት እና የአይጥ ዝርያዎች የመቆጣጠር ሥራ እስከ 2027 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ያስችላል።

ግምታዊ ዋጋ: $360,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

ቅዳሜና እሁድ የWar Memorial መዋኛ ገንዳዎች የሚሠሩበትን ሰዓታት የማራዘም ሥራ

ቅዳሜና እሁድ በWar Memorial መዋኛ ገንዳዎች ውስጥ መዋኘት የሚቻልባቸውን ሰዓታት የማርዘም ሥራ። መዋኛ ገንዳዎቹ ቅዳሜ ምሽቶች ላይ አንድ ሰዓት ዘግይተው የሚከፈቱ ሲሆን፣ እሁድ ጠዋቶች ላይ ደግሞ አንድ ሰዓት ቀደም ብለው የሚከፈቱ ይሆናል። ይህ ፕሮፖዛል ለተራዘመው የመዋኛ ሰዓት የሚውሉትን የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች ይሸፍናል።

ግምታዊ ዋጋ: $50,000

ቦታ: War Memorial መዝናኛ ማዕከል

   

የዛፎች እና የማኅበረሰብ የአትክልት ቦታዎች ጥበቃ ተሳትፎ አስተባባሪ

የዛፎችን እና የማኅበረሰብ አትክልት ቦታዎችን እንክብካቤ ፕሮግራም የማሳለጥ እና በጎ ፈቃደኞችን የማስተባበር ሥራን የሚያስኬድ አስተባባሪ የመቅጠር ሥራ። ይህ ለሦስት ዓመት የሚቆየው አዲሱ የሥራ ዘርፍ በሁሉም የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ነዋሪዎችን እውቀት እና እንቅስቃሴን የሚያሳድግ ነው።

ግምታዊ ዋጋ: $410,000

ቦታ: ከተማ-አቀፍ

   

ለCambridge Park ማሻሻያ የሚሆኑ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶችን የመገንባት ሥራ

የመናፈሻውን ተደራሽነት እና ንጽህና ጠንካራ የሆነ፣ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሕዝብ መጸዳጃ ቤት በመገንባት የማሻሻል ሥራ። ከዚህ ቀደም በPB የገንዘብ ድጋፍ የተሠሩ የPortland Loos (የPortland መጸዳጃ ቤቶች) ለFlagg Street እና Cambridge Common ዲዛይን በመደረግ ላይ ናቸው። ይህ የPB ፕሮፖዛል ተጨማሪ ቦታ ላይ ግንባታ እንዲካሄድ የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል።

ግምታዊ ዋጋ: $500,000

ቦታ: በሂደት ላይ ያለ ወይም በቅርቡ የሚደረግ የማኅበረሰብ መናፈሻ ቦታ እድሳት

   

የCambridge ነዋሪዎች ብስክሌት መግዛት እንዲችሉ እንርዳቸው

ይህ ፕሮፖዛል ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የብስክሌት ባለቤት መሆን የሚችሉባቸውን ዕድሎች ያሰፋል። ይህ ለሁለት ዓመት የሚቆየው ፕሮግራም ብስክሌቶች በቅናሽ ዋጋ የሚገዙበትን እና የተቸገሩ ነዋሪዎች አስተማማኝ የብስክሌት መጓጓዣ የሚያገኙበትን ሁኔታ ይፈጥራል።

ግምታዊ ዋጋ: $300,000

ቦታ: ከተማ-አቀፍ

   

የብስክሌት መጠገኛ ጣቢያዎችን የመጨመር እና ባሉበት ይዞት ጠብቆ የማቆየት ሥራ

በከተማዋ በሚገኙ የብስክሌት መጠገኛ ጣቢያዎች ላይ ጥገና ማካሄድ እና ባሉበት ሁኔታ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችል መደበኛ ፕሮግራም መቅረጽም ያስፈልጋል። ይህ ፕሮጀክት ይህንን ማድረግ የሚያስችለውን የሦስት ዓመት ፕሮግራም የሚያቋቁም ሲሆን፣ ተጨማሪ አምስት ጣቢያዎችን በመገንባት ጥቅም ላይ የሚውሉ መገልገያዎችን ያሰፋል፣ ሁሉም ሰው የብስክሌት መጠገኛ መሣሪያዎችንም ማግኘት እንዲችል ያደርጋል።

ግምታዊ ዋጋ: $85,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

የአሸዋ ቮሊቦል መጫወቻ ሜዳ

Buckingham Field ላይ ሙሉ የአሸዋ ቮሊቦል መጫወቻ ሜዳ እንዲሠራ ይደግፉ! ይህ ፕሮጀክት የማኅበረሰቡ አባላት አዝናኝ እና አስደሳች በሆነ መልኩ መተዋወቅ የሚችሉበትን ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በግንባታ ሂደቱም ላይ አሁን ካሉት የስፖርት ሜዳዎች ቦታ አይቀናነስም።

ግምታዊ ዋጋ: $100,000

ቦታ: Buckingham Field

   

Inman Square አካባቢ የሚገኘውን ነጻ የዋይፋይ አገልግሎት ተደራሽነት የማስፋፋት ሥራ

Inman Square ውስጥ በሚገኘው Mayor Alfred Vellucci መናፈሻ ውስጥ ነጻ የሕዝብ ዋይፋይ በመግጠም የኢንተርኔት ተደራሽነትን የማስፋፋት ሥራ።

ግምታዊ ዋጋ: $75,000

ቦታ: Inman Square ውስጥ በሚገኘው Alfred Vellucci መናፈሻ

   

ሁለት የአውቶብስ መጠለያዎችን የመገንባት ሥራ

በሁለት የአውቶቡስ ማቆሚያ ፌርማታዎች ላይ የአውቶብስ መጠለያዎችን የመሥራት ሥራ። ቦታዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የአውቶብስ ተጠቃሚዎች በሚጠቅም መልኩ ይመረጣሉ። ተደራሽ የሆኑ፣ ደኅንነታቸው የተጠበቁ እና ምቹ የሆኑ መጠለያዎችን ማቅረብ፣ ነዋሪዎች የሕዝብ ማመላለሻ እንዲጠቀሙ ያበረታታል፣ የከተማዋንም የአካባቢ ጥበቃ ግቦች ይደግፋል።

ግምታዊ ዋጋ: $400,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

ለአረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ማኅበረሰቦች የሚሆን የእንስሳት ሕክምና አገልግሎት ተዳራሽነትን የማስፋፋት ሥራ

የገንዘብ እና የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ነዋሪዎች የእንስሳት ሕክምና ተደራሽነትን የማሻሻል ሥራ። ይህ ፕሮፖዛል ለሦስት ዓመት የሚቆይ ነጻ ምርመራዎችን፣ የክትባት ክሊኒኮችን፣ የቤት እንስሳት እንክብካቤን፣ የጥርስ ሕክምናን እና የተንቀሳቃሽ ቫን አገልግሎቶችን ያቀርባል።

ግምታዊ ዋጋ: $200,000

ቦታ: ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው መኖሪያ ቤቶችን፣ የአረጋውያን መኖሪያ ተቋማትን እና ይህ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ሌሎች አካባቢዎችን ያካትታል።

   

ለመንገድ ዛፎች የሚሆኑ ቦታዎችን የማስፋት ሥራ

የእግረኛ መንገዶችን በማስወገድ ለአዳዲስ እና ነባር ዛፎች የሚሆኑ ቦታዎችን በማስፋት አካባቢያችንን ይርዱ። የእግረኛ መንገዶችን ማስወገድ ለዛፍ ሥሮች ተጨማሪ የአፈር ቦታ እንዲኖር ያደርጋል፣ ዛፎች ረጅም እና ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል፣ የፍሳሽ አካሄድን ያሻሽላል እንዲሁም የከተማ ሙቀትን ይቀንሳል።

ግምታዊ ዋጋ: $100,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

ነፃ የወር አበባ እንክብካቤ እና የሕፃናት ንጽህና ምርቶች

የንጽህና ምርቶች መግዛት የማይችሉ ሰዎች ከባድ ውሳኔዎች እንዲወስዱ ይገደዳሉ። የወር አበባ እና የንጽህና መጠበቂያ የሆኑ ምርቶች ዳይፐሮችን፣ የሕፃናት ንጽህና መጠበቂያ ሶፍቶችን (ዋይፕስ) እና ሌሎችንም በከተማዋ ሕንፃዎች ውስጥ የሚገኙ ምርቶች እንዲያካትቱ እና ለሦስት ዓመታት ያህል ተደራሽ መሆን እንዲችሉ ያግዙ።

ግምታዊ ዋጋ: $85,000

ቦታ: ባለቤትነታቸው የከተማው የሆኑ ንብረቶች (Cambridge Public Libraries (የCambridge የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት)፣ የእሳት አደጋ ክፍል፣ የከተማው መምሪያ ሕንፃዎች፣ የወጣቶች ማዕከላት)

   

የአካባቢው ሴቶች ያበረከቱትን ተሳትፎ የማክበር ሥራ፦ የCambridge Women's Heritage Project (የCambridge ሴቶች ቅርስ ፕሮጀክትን) የማጎልበት ሥራ

የተለያዩ የCambridge ሴቶች ያበረከቱዋቸውን፣ ተገቢውን እውቅና ያላገኙ አስተዋጽኦዎች አጉልቶ የማሳየት ሥራ። በልዩ ሁኔታ ተለይተው የሚቀረቡትን ሴቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ለማሳደግ የሚያስችል ለምርምር እና ለአፈ ታሪክ ቃለ-መጠይቆች የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ የማቅረብ ሥራ። ከትምህርት ቤቶች እና ቤተ-መጻሕፍቶች ጋር የሚደረገውን ትብብር ለማሳደግ አሁን ላይ ያለውን የፕሮጀክት ድረ-ገጽ እንደገና ዲዛይን የማድረግ ሥራ።

ግምታዊ ዋጋ: $60,000

ቦታ: የCambridge ድረ-ገጽ

   

የእግረኞችን ደኅንነት ማሻሻል

ወደ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ወደ አረጋዊያን መኖሪያ ተቋማት ለመሄድ የእግረኛ መንገዱን የሚጠቀሙ ሰዎች የተሻለ ደኅንነት እንዲኖራቸው የማድረግ ሥራ። ይህ ፕሮጀክት ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ለማድረግ የሚያግዙ ከፍ ያሉ የእግረኛ መንገዶች፣ ኢንተራክቲቭ የፍጥነት ገደብ ምልክቶች እና ብልጭ ድርግም የሚሉ የእግረኛ መሻገሪያ ምልክቶች እንዲገጠሙ ያደርጋል።

ግምታዊ ዋጋ: $400,000

ቦታ: የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና የአረጋዊያን መኖሪያ ተቋማት

   

ለስማርት ሪሳይክሊንግ እና ለቆሻሻ መዳመጫዎች

Cambridge ውስጥ የአይጥ ዝርያዎችን የሚቋቋሙ፣ ከንክኪ ነጻ የሆኑ ሪሳይክል የማድረግ ሥራን የሚሠሩ 15 የቆሻሻ መዳመጫዎችን የመጨመር ሥራ። "Big Belly" የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች የከተማዋን ጽዳት ይጠብቃሉ፣ የአይጦችን ቁጥር ይቀንሳሉ፣ ሪሳይክል የማድረግ ልምድንም ይጨምራሉ።

ግምታዊ ዋጋ: $120,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል

   

በሞቃታማ መንገዶች ላይ የሚሠሩ መጠለያ የተገጠመላቸው መቀመጫዎች

መጠለያ እና መቀመጫ በሚያስፈጉባቸው፣ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ከ3-5 የሚሆኑ መጠለያ የተገጠመላቸው መቀመጫዎች የመገንባት ሥራ። እያንዳንዱ አካባቢ ከ300 እስከ 500 square feet (ካሬ ጫማ) የሚሆን ስፋት የሚኖረው ሲሆን፣ የጥላ ሸራዎችን እና ለመቀመጫነት የሚጋብዙ እንደ ዥዋዥዌ ወንበሮች፣ መቀመጫዎች፣ ጠረጴዛዎች እና የጋራ መቀመጫዎች አካትተው ይይዛሉ።

ግምታዊ ዋጋ: $450,000

ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽእኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል