Cambridge ውስጥ አዝናኝ መጫወቻ ቦታዎችን መሥራት |
ጥላ ሊሆኑ የሚችሉ ግንባታዎችን እና መቀመጫ የሚሆኑ ወንበሮችን በመገንባት መናፈሻዎችን ማሻሻል |
በከተማው መናፈሻዎች የሚሰጡ ነፃ የፀሐይ መከላከያ ቅባቶች |
ትልቅ እናልም፦ የሕዝብ የSTEAM ፕሮግራሞች |
በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በነፃ የሚታደል ቅጫም ማስለቀቂያ ማበጠሪያዎች |
የሕፃናት ቁሳቁሶችን የያዙ ለአዲስ ወላጆች የሚሆኑ የእንኳን ደስ ያለዎት ሳጥኖች (ጥቅሎች) |
የከተማ ስብሰባዎች የቀጥታ ስርጭት የጽሑፍ መግለጫ ተደራሽነት |
ተንቀሳቃሽ የቤት እንስሳ እንክብካቤ አገልግሎት |
የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ መገንባት |
መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል አስቸጋሪ የሆኑ እቃዎችን የሚሰበሰብ ተንቀሳቃሽ ማዕከል |
ስለት ላላቸው እቃዎች የሚሆኑ ደኅነታቸው የተጠበቁ ቆሻሻ መጣያዎች መሥራት |
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የባትሪ ኃይል መሙያዎች |
የቅርጫት ኳስ ሜዳ ማሻሻያዎች |
የሴት ሕፃናት አቅም ማጎልበቻ ስፖርታዊ ዝግጅቶች |
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክለቦች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ |
የMoses Youth Center ማሻሻያ |
ማስታወሻ: እነዚህ ፕሮጀክቶች በዘፈቀደ ቅደም ተከተል የተዘረዘሩ ናቸው።
Cambridge ውስጥ አዝናኝ መጫወቻ ቦታዎችን መሥራት
ለCambridge ሕፃናት የሚሆኑ አዝናኝ መጫወቻ ቦታዎችን እንገንባ! አካላዊ እንቅስቃሴ የተቀላቀለበት ጨዋታ ሕፃናት በቅርብ ክትትል ውስጥ ሆነው እየተጫወቱ መዝናናት እንዲችሉ ያድርጋል። የማኅበረሰቡ አጋር የሆኑ አገልግሎት አቅራቢዎች በሚያዘጋጇቸው ዝግጅቶች እና ሥልጠናዎች አማካኝነት የሕፃናት አዕምሮ ዓይነ-ህሊናን (ኢማጅኔሽን) የሚያሳድ አዲስ ዓይነት የመጫወቻ ቦታ (ጨዋታ) ይዘጋጃል።
ግምታዊ ዋጋ: $150,000
ቦታ: በመላው Cambridge ከተማ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በነፃ የሚታደል ቅጫም ማስለቀቂያ ማበጠሪያዎች
የቅጫም ወረርሺኞች በሚከሰቱ ጊዜ ተጠቂ ቤተሰቦች የሚያወጡትን ወጪ ለማቃለል ታስቦ በነፃ የሚታደሉ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ቅጫም ማስለቀቂያ ማበጠሪያዎች። እነዚህ ማበጠሪያዎች ቅጫም ለማስለቀቅ በሚደረገው የእጥበት ሕክምና ወቅት ከመደበኛዎቹ ማበጠሪያዎች ይልቅ እጅግ ውጤታማ እንዲሆኑ በሚያደርግ መልኩ ጥቅጥቅ ተደርገው የተሠሩ ናቸው።
ግምታዊ ዋጋ: $60,000
ቦታ: በሁሉም የCambridge የሕዝብ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።
የሕፃናት ቁሳቁሶችን የያዙ ለአዲስ ወላጆች የሚሆኑ የእንኳን ደስ ያለዎት ሳጥኖች (ጥቅሎች)
አዲስ ወላጆችን እንደግፍ! የሕፃናት ቁሳቁሶች ውድ ናቸው፤ አዲስ ለተወለደ ሕፃን እንክብካቤ መስጠትም ከባድ ነው። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ለአዳዲስ ወላጆች የሕፃናት ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ወላጅ ወደመሆን በቀላሉ እንዲሸጋገሩ በሚያግዙ የማኅበረሰቡ ሀብቶች ዙሪያም ወላጆቹ መረጃ እንዲያገኙ ያደርጋል።
ግምታዊ ዋጋ: $60,000
ቦታ: በቤተሰቦች ማዕከል በኩል በከተማ አቀፍ ደረጃ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
የከተማ ስብሰባዎች የቀጥታ ስርጭት የጽሑፍ መግለጫ ተደራሽነት
በከፊልም ሆነ በሙሉ መስማት ለተሳናቸው ሰዎች የሕዝብ ስብሰባዎችን ይበልጥ ተደራሽ እና ለመታደም ምቹ እንዲሆንላቸው እናድርግ! ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ በከተማ አስተዳደሩ በባለቤትነት በተያዙ ሕንፃዎች ውስጥ የሚካሄዱ የሕዝብ ስብሰባዎችን በቀጥታ ስርጭት የጽሑፍ ግልባጭ ለማዘጋጀት የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ስክሪኖችን እና የሰው ኃይልን ለማቅረብ ድጋፍ ያደርጋል።
ግምታዊ ዋጋ: $250,000
ቦታ: በከተማ አስተዳደሩ በባለቤትነት በተያዙ ሕንፃዎች እና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ተንቀሳቃሽ የቤት እንስሳ እንክብካቤ አገልግሎት
የገንዘብ ወይም እንቅስቃሴ ከማድረግ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች ላሉባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የእንስሳት ሕክምና ተደራሽነትን የማሻሻል ሥራ ይሠራል። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ነፃ የሕክምና ክትትል፣ የክትባት ክሊኒኮች፣ የንጽሕና እና ውበት መጠበቂያ፣ የጥርስ ሕክምና እና ሌሎች አገልግሎቶች ለሚያስፈልጋቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የቤት እንስሶች ያቀርባል።
ግምታዊ ዋጋ: $200,000
ቦታ: ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው መኖሪያ ቤቶች፣ በአረጋዊያን መኖሪያ ተቋማት እና በሌሎች ቦታዎች እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ መገንባት
የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆኑ የአበባ ቦታዎች በውስጣቸው፣ ለአካባቢው የድር እንስሳት የሚሆኑ ዘሮችን የሚያቀርቡ በአካባቢው የሚበቅሉ የእፅዋት ዝርያዎችን ይይዛሉ። ይህ ፕሮጀክት የአካባቢውን አበባዎች ለማርባት ዘር በመበተን አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታን በከተማዋ መናፈሻ ላይ በመገንባት፣ በአካባቢው የሚገኙ ዘር በታኝ እንስሳዎችን ለመሳብ እና ለመመገብ ይጠቅማል!
ግምታዊ ዋጋ: $75,000
ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽዕኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል።
መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል አስቸጋሪ የሆኑ እቃዎችን የሚሰበሰብ ተንቀሳቃሽ ማዕከል
እቃዎችን ይዘው መልሶ ጥቅም ላይ ወደሚያውላቸው ማዕከል ከመጓዝዎ ይልቅ ማዕከሉ ወደ እርስዎ ይምጣልዎ! በማኅበረሰብ ዝግጅቶች ወቅት ይህ ተንቀሳቃሽ ማዕከል የከተማዋ ነዋሪዎች እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ከተማዋን መሻገር ሳይኖርባቸው መልሰው ጥቅም ላይ ማዋል እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ኤሌክቶኒክ ቆሻሻዎችን፣ መጽሓፍቶችን፣ ባትሪዎችን፣ ፕላስቲኮችን እና ሌሎችንም መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል እገዛ ያቀርባል።
ግምታዊ ዋጋ: $75,000
ቦታ: በከተማው ዙሪያ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ስለት ላላቸው እቃዎች የሚሆኑ ደኅነታቸው የተጠበቁ ቆሻሻ መጣያዎች መሥራት
ትልቅ እና ትንሽ መርፌዎችን ወይም ሌሎች ስለታም የሕክምና መሣሪያዎችን ደኅንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ለማስወገድ የሚያስችሉ ቆሻሻያ መጣያ ሳጥኖችን መሥራት። እነዚህ የቆሻሻ ሳጥኖች በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ፍላጎት በሚኖርባቸው ቦታዎች ላይ ስለት ያላቸውን ዕቃዎች ይበልጥ ደኅንነቱ በተጠበቀ እና ምቹ በሆነ የማስወገጃ አማራጮችን ያቀርባል።
ግምታዊ ዋጋ: $30,000
ቦታ: ከፍተኛ ፍላጎት በሚኖርባቸው ስድስት ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የባትሪ ኃይል መሙያዎች
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) ባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን በከተማዋ 3 ቦታዎች ላይ የሚሠሩ ሲሆን፣ 10 የባትሪ ኃይል መሙያዎችን ይዘውም ይሠራሉ። የEV ተሽከርካሪዎች ብዛት ቀስበቀስ እየጨመረ መሆኑን በከተማው ውስጥ ከሚገኙ ባትሪ መሙያ ጣቢያዎች አስተዳደሩ የሰበሰበው መረጃ ያመላክታል። ይህ የፕሮጀክት ሃሳብ ተጨማሪ ለሕዝብ ተደራሽ የሆኑ የEV ባትሪ መሙያ ጣቢያዎችን እንደሚፈልጉ ያመላከቱ ነዋሪዎች ላነሱት ጠንካራ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል።
ግምታዊ ዋጋ: $200,000
ቦታ: በሂደት በሚወሰኑ የከተማዋ 3 ቦታዎች ላይ የሚሠሩ 10 የባትሪ ኃይል መሙያዎች።
የቅርጫት ኳስ ሜዳ ማሻሻያዎች
ከቤት ውጪ የሚገኙ የቅርጫት ኳስ ሜዳዎችን ማሻሻል! ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው በሚገኙ ማሻሻያ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ የቅርጫት ኳስ ሜዳ የመሬት እድሳት ይሠራል፣ መስመሮችን እንደ አዲስ ይቀባል፣ በተጨማሪም ሜዳውን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች መጠቀም እንዲችሉ ከፍ ዝቅ የሚል የቅርጫት ኳስ ቀለበት ይገጥማል።
ግምታዊ ዋጋ: $350,000
ቦታ: በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና ተጽዕኖ ዙሪያ የሚደረጉ ግምገማዎችን መሠረት በማድረግ የሚወሰን ይሆናል።
የሴት ሕፃናት አቅም ማጎልበቻ ስፖርታዊ ዝግጅቶች
የCambridge Sports for Girls Night በአንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ሴት ሕፃናት የሚሆኑ በርካታ ዝግጅቶችን እንዲያካትት ማድረግ። እነዚህ አዝናኝ ዝግጅቶች ሴት ሕፃናት ወይም ወጣቶች የማኅበረሰብ ድጋፍ በሚያገኙበት መቼት ውስጥ የተለያዩ ስፖርቶችን መሞከር እንዲችሉ ያደርጋሉ!
ግምታዊ ዋጋ: $45,000
ቦታ: በWar Memorial፣ Danehy Park፣ በCPS ትምህርት ቤት ጂምናዚየሞች እና በሌሎች ቦታዎች ላይ እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክለቦች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ
በCRLS የሚገኙ የተማሪ ክበቦች በአሁኑ ጊዜ ለማኅበረሰባችን ብዙ ጥሩ ነገሮችን ያደርጋሉ፦ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ አጋዥ ትምህርት፣ ትምህርታዊ እና ሙያዊ ማጎልበቻ ፕሮግራሞች እና ሌሎችንም ያደርጋሉ። እነዚህ ክለቦች ለማኅበረሰቡ እና ከዚህም አልፈው ለሚገኙ ሰዎች ሊያበረክቱ የሚችሉትን መልካም ነገሮች የሚያሳድግ አቅም እንዲኖራቸው የገንዘብ ድጋፍ እናቅርብላቸው!
ግምታዊ ዋጋ: $150,000
ቦታ: በCambridge Rindge and Latin ትምህርት ቤት እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ለአዋቂዎች የሚሆኑ አዝናኝ፣ ትምህርታዊ የብስክሌት ዝግጅቶች
ለአዋቂዎች የሚሆኑ የብስክሌት ግልቢያ መማሪያ እና የከተማ ውስጥ የብስክሌት ግልቢያ መሠረታዊ እውቀት ማስጨበጫ ወክሾፖችን በማቅረብ የከተማዋን የብስክሌት ደኅንነት ትምህርት አማራጮች ማስፋት። ተጨማሪ የትምህርት ዕድሎች መኖራቸው፣ በከተማዋ ውስጥ ብስክሌት መጋለብ የሚያስችል ደኅንነት እንዳለ ተሰምቷቸው ተጨማሪ ሰዎች መጋለብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
ግምታዊ ዋጋ: $110,000
ቦታ: በሕዝብ መናፈሻዎች፣ ባዶ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች፣ በብስክሌት መንገዶች ላይ እስከ 2 ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ለሕዝብ ዝግጅቶች በቀላሉ ተደራሽ የሆኑ ምንጣፎች
Cambridge ውስጥ በየዓመቱ ብዙ ከቤት ውጪ የሚዘጋጁ ዝግጅቶች አሉ። ለእንቅስቃሴ ምቹ ተደርገው የሚዘጋጁ ምንጣፎች ወጣ ገባ በሆኑ መሬቶች ላይ በመነጠፍ፣ እነዚህ ዝግጅቶች የሚዘጋጁባቸውን ውብ አረንጓዴ ሥፍራዎች ተጨማሪ ሰዎች ማየት እንዲችሉ ዕድሉን ይከፍታሉ። እነዚህ ምንጣፎች የሕፃናት ጋሪዎች፣ ተሽከርካሪ ወንበሮች እና ሌሎች የእንቅስቃሴ ድጋፍ የሚሰጡ መሣሪያዎች የሚጠቀሙ ቤተሰቦችን ይደግፋሉ።
ግምታዊ ዋጋ: $20,000
ቦታ: በከተማው ውስጥ ከቤት ውጪ ለሚዘጋጁ ዝግጅቶች እስከ ሦስት ዓመት ለሚዘልቅ ጊዜ።
ደኅንነታቸው የተጠበቁ ጎዳናዎች እንዲኖሩን ፍጥነት መቀነስ
የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ 48 ፍጥነት መቀነሻ ጉብታዎችን ቁልፍ በሚባሉ የCambridge ጎዳናዎች ላይ መገንባት። ፍጥነት የሚቀንሱ ጉብታዎች የእግረኞችን ደኅንነት የሚጨምሩ ሲሆን፣ ለኑሮ ምቹ እና ደኅንነታቸው የተጠበቁ መኖሪያ ስፍራዎችንም ለመፍጠር ያግዛሉ። ይህ ፕሮጀክት ከፍጥነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታት እና አጠቃላይ የመንገድ ደኅንነትን ለማሻሻል ያለመ ነው።
ግምታዊ ዋጋ: $250,000
ቦታ: ከአውራ ጎዳናዎች ጋር በመስቀለኛ በሚገናኙ ንዑስ መንገዶች።