| የወደፊት ሕይወቴን በድምጼ አቀናለሁ |
| ለቅዝቃዜ እና ለዝናብ የሚሆኑ ብርድ እና እርጥበት የሚከላከሉ ቁሳቁሶች |
| የትራንስፖርት እገዛ አገልግሎት |
| የትምህርት ቤት አቅርቦቶች ቀጣይነት ያለው ተደራሽነትን መደገፍ |
| የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲያድጉ የሚደግፉ ቦታዎች |
| በእግረኛ መንገዶች ላይ ለተተከሉ ዛፎች የአበባ ማስቀመጫዎችን ማቅረብ |
| ከመኖሪያ ቤቶች የአይጥ ችግርን የሚያጠፋ/የሚቆጣጠር ፕሮግራም |
| ዝናብ ፍሳሽ ማመቂያ እና መቆጣጠሪያ እንዲሁም ዘር በመበተን አበባዎችን ለማርባት አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ ግንባታ |
| በተውሶ ሊገለገሉባቸው የሚችሉ ከቤት ውጪ ያሉ ስፍራዎችን መንከባከብ የሚያስችሉ መሣሪያዎች |
| የRiverside Press Park የማኅበረሰብ አትክልት ቦታ ማሻሻያ |
| ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ነጻ ብስክሌቶች |
| ለብስክሌት መንገዶች የሚሆኑ የኮንክሪት መከለያ ግንቦች |
| የጎዳናዎችን ደኅንነት ለመጠበቅ የሚሠሩ ማሻሻያዎች |
| የእግረኛ መንገዶችን ማስተካከል፣ ዛፎችን መንከባከብ |
| የብስክሌት ቆጣሪዎች |
ማስታወሻ: እነዚህ ፕሮጀክቶች በዘፈቀደ ቅደም ተከተል የተዘረዘሩ ናቸው።
ለቅዝቃዜ እና ለዝናብ የሚሆኑ ብርድ እና እርጥበት የሚከላከሉ ቁሳቁሶች
የማኅበረሰባችን አባል የሆኑ መኖሪያ ቤት የሌላቸው ግለሰቦች በቀዝቃዛ እና እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ወቅት ደኅንነታቸውን እንዲጠብቁ የሚያግዙ ሙቀት የሚሰጡ እና እርጥበት የማያስገቡ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ቁሳቁሶቹ ሙቀት የሚሰጡ ልብሶችን፣ የዝናብ መከላከያ ካፖርቶችን፣ የአየር ሁኔታ ለውጥ የሚቋቋሙ የእንቅልፍ ከረጢቶችን እንዲሁም ጠንካራ ቡትስ ጫማዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
ግምታዊ ዋጋ: $60,000
ቦታ: በከተማ አቀፍ ደረጃ ለ3 ዓመታት
ዝናብ ፍሳሽ ማመቂያ እና መቆጣጠሪያ እንዲሁም ዘር በመበተን አበባዎችን ለማርባት አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ ግንባታ
Cambridge ውስጥ ተጨማሪ የዝናብ ፍሳሽ ማመቂያ እና መቆጣጠሪያ እንዲሁም ዘር በመበተን አበባዎችን ለማርባት አስተዋጽዖ ለሚያደርጉ እንስሳት የሚሆን የአበባ ቦታ እንገንባ! ንቦችን እና ቢራቢሮዎችን የሚስቡ ሲሆን፣ ከአውሎ ነፋሶች እና ኃይለኛ ዝናቦች በኋላ የሚፈጠረውን ኩሬ ለመቀነስ ያግዛሉ።
ግምታዊ ዋጋ: $100,000
ቦታ: በፍላጎት እና በሚያሳድረው ተጽዕኖ ግምገማ መሠረት ይወሰናል።
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ነጻ ብስክሌቶች
ተጨማሪ የCambridge ነዋሪዎች አስተማማኝ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ የመጓጓዣ አማራጭ እንዲያገኙ ለማስቻል የብስክሌት ቫውቸር ፕሮግራሙን ያስፋፋል። ይህ ፕሮግራም ነዋሪዎች በፔዳል የሚነዱ ብስክሌቶችን፣ ኢ-ብስክሌቶችን፣ ጭነት መያዝ የሚያስችሉ ብስክሌቶችን ወይም ለአካል ጉዳተኞች ተስማሚ ተደርገው የተሠሩ (አዳፕቲቭ) ብስክሌቶችን እንዲገዙ ቫውቸሮችን ያቀርባል።
ግምታዊ ዋጋ: $150,000
ቦታ: በከተማ አቀፍ ደረጃ ለ3 ዓመታት።
የእግረኛ መንገዶችን ማስተካከል፣ ዛፎችን መንከባከብ
በዛፎች አቅራቢያ ያሉ ያልተስተካከሉ ወይም የተበላሹ የእግረኛ መንገዶችን ያድሳል። ጫና የሚቋቋም መንገድ ወይም ሌሎች አስፈላጊ እድሳቶችን በመጠቀም የጥገና ሥራዎቹ ይከናወናሉ። ጥገናዎቹ የዛፍ ሥሮቹ እንዲያድጉ የሚያስችል ቦታ እንዲኖራቸው የሚሰጡ ሲሆን፣ የእግረኛ መንገዶቹንም ለሁሉም ሰው ደኅንነታቸው የተጠበቁ እና ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል።
ግምታዊ ዋጋ: $100,000
ቦታ: በፍላጎት እና በሚያሳድረው ተጽዕኖ ግምገማ መሠረት ይወሰናል።
የብስክሌት ቆጣሪዎች
በከተማው ውስጥ ቋሚ እና የአጭር ጊዜ የብስክሌት ቆጣሪዎችን ያስቀምጣል። የብስክሌት ቆጠራ ጣቢያዎች ለከተማው የሕዝብ ፖሊሲዎችን እና ፕሮጀክቶችን ለማውጣት የሚያስችሉ መረጃዎችን ይሰበስባሉ። መረጃው ወደፊት ለሚገነቡ የብስክሌት መንገድ ሥራዎች የመረጃ ግብዓት የሚሆን ሲሆን፣ ከተማ አስተዳደሩም መንገድን የሚጠቀሙ ሁሉም ተጠቃሚዎች ፍላጎታቸውን መሟላቱን ማረጋገጥ ያስችለዋል።
ግምታዊ ዋጋ: $209,000
ቦታ: በፍላጎት እና በሚያሳድረው ተጽዕኖ ግምገማ መሠረት ይወሰናል።
የቅርጫት ኳስ ሜዳ ማሻሻያዎች
Cambridge ውስጥ የሚገኙ የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች በማኅበረሰቡ አዘውትረው አገልግሎት ላይ ስለሚውሉ የማርጀት ምልክቶች ሊታዩባቸው ይችላሉ። የገንዘብ ድጋፉ በከተማው ውስጥ ባሉ የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች ላይ የማሻሻያ ሥራዎች እንዲካሄዱ ድጋፍ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ሜዳዎቹም ደኅንነታቸው የተጠበቁ፣ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ እንዲሁም ለሁሉም ዕድሜዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል።
ግምታዊ ዋጋ: $250,000
ቦታ: በፍላጎት እና በሚያሳድረው ተጽዕኖ ግምገማ መሠረት ይወሰናል።
ለዋናተኞች የተዘጋጁ ማድረቂያ ቦታዎች እና የመዋኛ ገንዳ ማጽጂያ መሣሪያዎች
በከተማ አስተዳደሩ ይዞታ ሥር ላሉ የመዋኛ ገንዳዎች የመዋኛ ልብስ ማድረቂያዎችን እና አዲስ የመዋኛ ገንዳ ማጽጂያ መሣሪያዎችን ይገዛል። መሣሪያዎቹ መንጠሪያ ስፕሪንጎችን፣ መዋኛ ነጠላ ጫማዎችን (ፍሊፕሮች) እና የተሻሻሉ የሻወር ዕቃዎችን ያካትታሉ። ይህ ለሁሉም ሰው በመዋኛ ገንዳዎቻችን አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀላል እና የበለጠ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
ግምታዊ ዋጋ: $20,000
ቦታ: በWar Memorial & Gold Star መዋኛ ገንዳዎች።
የክረምት ጊዜ በአዳራሽ ውስጥ የሚካሄዱ መዝናኛ ዝግጅቶች
በቀዝቃዛው የክረምት ወቅት ላይ ልጆች እና ቤተሰቦች የሚጫወቱባቸው ተጨማሪ ቦታዎች ያስፈልጋሉ። በክረምት ወቅት በተለያዩ የወጣቶች ማዕከላት እየተዘዋወሩ ሙቀት ባለው አዳራሽ ውስጥ በወር አንድ ጊዜ ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚካሄዱ፣ ሁሉም ሰው መጥቶ መጫወት የሚችልባቸውን ክፍት የጨዋታ ሰዓቶች እናቅርብ። ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ከአዋቂ ሰው ጋር መምጣት አለባቸው።
ግምታዊ ዋጋ: $30,000
ቦታ: የCambridge ወጣጦች ማዕከላት
የውጪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሣሪያዎች
ከቤት ውጭ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሥራት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን በፓርክ ውስጥ በመትከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን እና ጤንነትን መጠበቅን የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን እናድርግ! ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሆኑ መሣሪያዎች የተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩ እና በሌሎች የፓርኩ መገልገያዎች ላይ የሚደርሰውን እርጅና እና መበላሸት ለመቀነስ ይረዳሉ።
ግምታዊ ዋጋ: $150,000
ቦታ: በፍላጎት እና በሚያሳድረው ተጽዕኖ ግምገማ መሠረት ይወሰናል።