እንኳን ወደ Cambridge ከተማ አስተዳደር Participatory Budgeting (PB) ዑደት 11 ድምጽ መስጫ በደህና መጡ!
ከማርች 6-16 ቀን 2025 ዓ.ም
የCambridge ከተማ አስተዳደር ሁሉንም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ነዋሪዎች በከተማዋ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ላይ ድምጽ እንዲሰጡ ይጋብዛል። የከተማዋ $1 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል በጀት ምን ላይ መዋል እንዳለበት ድምጽ በመስጠት መወሰን ይችላሉ!
በከተማ አቀፍ ደረጃ ድምጽ የመስጠት ሂደቱ ከማርች 6-16 ቀን 2025 ዓ.ም ይካሄዳል።
ድምጽ ለመስጠት የማረጋገጫ ኮድ ያስፈልግዎታል። ኮዱን በጽሑፍ መልዕክት፣ በኢይሜል ወይም በድምጽ መስጫ ጣቢያ በአካል በመቅረብ መቀበል ይችላሉ።
የጽሑፍ መልዕክት መቀበል የሚችል ሞባይል ስልክ ካለዎ፣ ድምጽ መስጠት ለመጀመር እባክዎ "አሁን ድምጽ ይስጡ!" የሚለውን ቁልፍ ይምረጡ።
ሞባይል ስልክ ከሌለዎ ኮዱን በኢሜይል መቀበል ይችላሉ። እባክዎ የተደራሽነት ኮዱን ለማግኘት እና ድምጽ ለመስጠት የ"ኮድ ለማስገባት" የሚለውን ቁልፍ ይምረጡ እና በገጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።
በአካል ለመምረጥ ከፈለጉ ሙሉውን የድምጽ መስጫ መርሃ ግብር እና የጣቢያዎቹን ዝርዝር ለማየት pb.cambridgema.gov ድር-ገጽን ይጎብኙ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ pb.cambridgema.gov ድረ-ገጽን ይጎብኙ። ለማንኛውም ጥያቄ Budget Office (የበጀት ቢሮውን) በpb@cambridgema.gov ወይም (617) 349-4270 ያግኙ።
ይህ ድረ-ገጽ የተበለጸገው በStanford Crowdsourced Democracy Team ነው።
https://www.cambridgema.gov/participatorybudgeting