Pickleball እንጫወት |
የ Bluebikes ተደራሽነትን ማስፋፋት |
ስማርት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች |
የ Moore Youth Center የውጪውን ክፍል ማሻሻል |
የቅርጫት ኳስ እደሳ |
የብስክሌት ፓርኪንግ እና የብስክሌት መጠገኛ ጣቢያዎች |
የ E-cargo ብስክሌቶች ዛፎችን ውሃ ለማጠጣት |
መጫወቻ ቦታዎች ላይ የእይታ መግባቢያ ቦርዶች |
የራስ ሰር በሮች ለቤተ መጽሐፍቶች |
ሶስት አዲስ የህዝብ አርት ምስሎች |
በ Danehy ፓርክ ላይ መንገድዎን መፈለግ |
ይመልከቱ እና ያድምጡ፦ አስተማማኝ መሸጋገሪያ ለ Cambridge |
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች |
የውጪ ጂም |
ቼዝ እንጫወት |
ተጨማሪ ከቤት ውጪ የህዝብ Wi-fi |
ለ Danehy ፓርክ እና ለ Cambridge ዛፎች |
Cambridge ን ለመጎብኘት የዲጂታል Map (ካርታ) |
ቴክኖሎጂ ለወጣት ማዕከላት |
በጥላው ውስጥ ይቀመጡ እና ቻርጅ ያድርጉ |
ማስታወሻ: እነዚህ ፕሮጀክቶች በዘፈቀደ ቅደም ተከተል የተዘረዘሩ ናቸው።
ስማርት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ እና የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች
በ Cambridge ውስጥ 5 ንክኪ የሌላቸው አይጦችን የሚቋቋም “Big Belly” መልሶ ጥቅም ላይ ማዋያ እና ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ይጨምሩ። Big Belly ማጠራቀሚያዎች በሶላር የሚሰሩ እና ከባህላዊ ማጠራቀሚያዎች የበለጠ ውጤታማ ናቸው። ከተማው የበለጠ ንጹህ እንዲሆን ያደርጋሉ፣ አይጦችን ይቀንሳሉ፣ እና መልሶ በጥቅም ላይ ማዋል እንዲጨምር ያደርጋሉ።
ግምታዊ ዋጋ: $40,000
ቦታ: በፍላጎት እና በተጽዕኖ ግምገማ መሰረት ለመወሰን።
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች በሁለት ቦታዎች ይግጠሙ። የኤሌክትሪክ መኪናዎች በጣም ታዋቂ እየሆኑ ነው፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው በቤቱ ቻርጅ አያደርግም። የህዝብ ቻርጀሮች የኤሌክትሪክ መኪናን ያበረታታል እናም አካባቢያችንን ይጠቅማል።
ግምታዊ ዋጋ: $250,000
ቦታ: በፍላጎት እና በተጽዕኖ ግምገማዎች ለመወሰን። ኢላማ የተደረገባቸው ቦታዎች የማዘጋጃ ቤት የመኪና ማቆሚያን፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ያላቸው መንገዶች፣ እና የሚፈለጉ ቦታዎች ያካትታሉ።
Cambridge ን ለመጎብኘት የዲጂታል Map (ካርታ)
በህዝብ ጉብኝት ላይ እገዛ ለማድረግ የዲጂታል ምልክትን ይግጠሙ። ይህ ፕሮጀክት የመንገድ map (ካርታ) ን ያቀርባል፣ የህዝብ መጓጓዣ መንገዶችን እና የማህበረሰብ ቦታዎችን (ቤተ መጽሐፍት፣ ፓርኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ወዘተ.) ይዘረዝራል፣ እና ስለወደፊት ዝግጅቶች እና አስፈላጊ ማስታወቂያዎች አስፈላጊ ማስታወቂያዎች መረጃን ያካትታል።
ግምታዊ ዋጋ: $60,000
ቦታ: በዋና squares (ጎዳናዎች) አቅራቢያ እንደ የመሸጋገሪያ ቦታ ጣቢያዎች ያሉ በጣም የተጨናነቁ ቦታዎች።
በጥላው ውስጥ ይቀመጡ እና ቻርጅ ያድርጉ
በ Cambridge ዙሪያ ከሶላር ሃይል ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ጋር 10 ጥላ ያላቸውን መቀመጫዎች ይግጠሙ። ይህ ፕሮጀክት የእግረኞችን የቀን ከቀን የኑሮ ጥራትን ያሻሽላል። እነዚህ የሶላር መቀመጫዎች ሰዎች ጸሃይ በሌለበት ቦታ እንዲቀመጡ እና የኤሌክትሮኒክ መሳሪያቸውን ቻርጅ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
ግምታዊ ዋጋ: $100,000
ቦታ: በፍላጎት፣ በተጽዕኖ፣ እና በቦታ መኖር የሚወሰን ነው። የሚመከሩ ቦታዎች ፓርኮችን እና የከተማ squares (ጎዳናዎች) ን ያካትታሉ።