እንኳን ወደ Cambridge ከተማ አስተዳደር Participatory Budgeting (PB) (አሳታፊ በጀት ማድረጊያ) ድምጽ መስጫ በደህና መጡ!
የCambridge ከተማ አስተዳደር ሁሉንም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆናቸው ነዋሪዎች በከተማዋ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች ላይ ድምጽ እንዲሰጡ ይጋብዛል። የከተማዋ $2 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል በጀት ምን ላይ መዋል እንዳለበት ድምጽ በመስጠት መወሰን ይችላሉ!
ድምጽ የመስጠ ሂደቱ ከማርች 7 እስከ 17 ቀን 2024 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
ወደ ድምጽ መስጫ ገጹ ለመሄድ እባክዎ "አሁኑኑ ድምጽ ይስጡ!" የሚለውን ሊንክ ይምረጡ። በኦንላይን ድምጽ የመስጫ ቅጹን በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በቤንጋሊ፣ በቻይንኛ፣ በሄይቲ ክሪኦል፣ በፖርቱጋልኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል። የጽሑፍ መልእክት መቀበል የሚችል ስልክ ካለዎ፣ እዚህ ጋር ድምጽ መስጠት ይችላሉ።
ስልክ የሌለዎት ሆኖ ድምጽ መስጠት ግን የሚፈልጉ ከሆነ፣ የመግቢያ ኮድ ለማግኘት እና ድምጽ ለመስጠት ከታች ያለውን "ኮድ አስገባ" የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። እባክዎ ለቤተሰብዎ ከአንድ በላይ ኮዶች ካስፈለጉዎ፣ በpb@cambridgema.gov ኢሜይል አድራሻ ወደ Budget Office (በጀት ቢሮው) ኢሜይል በመላክ መጠየቅ ይችላሉ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክዎ pb.cambridgema.gov ድረ-ገጽን ይጎብኙ። አልያም ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ pb@cambridgema.gov ወይም (617) 349-4270ን በመጠቀም Budget Officeን ማግኘት ይችላሉ።
*ሁሉም የ Cambridge የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመምረጥ ብቁ ናቸው።